የቅድስት ሥላሴ

Holy Trinity

ኑ እናመስግን

Lyrics

ኑ እናመስግን በዝማሬ በእልልታ

ጠላት ዲያብሎስን በሞቱ ለረታ

ከእኛ ጋር ነውና የሠራዊት ጌታ

ጨለማው ኑሮ የስደት ሕይወት

በእግዚአብሔር ፍቅር ብርሃን በራበት

ባርነት ቀርቶ ነጻነት ወጣን

ልመናችንን እግዚአብሔር ሰማን

መሰናክሉን ክፉውን ፈተና

አልፈነው መጣን በአምላክ ጎዳና

አምላክ ከእኛ ጋር ስለነበረ

ዲያብሎስ አፍሮ ተዋርዶ ቀረ

ሚያሰጨንቀን ዛሬ ተፈታ

የሕዝቡን ዕንባ አበሰ ጌታ

በምሕረቱ ስለጎበኘን

አምላካችንን ኑ እናመስግን

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening