✦
የቅድስት ሥላሴ
•Holy Trinity
ተነሡ እንዘምር
Lyrics
ተነሡ እንዘምር /2/
በአንድነት ሆነን በእልልታ /2/ ኧኸ /3/
ምስጋና በሰማይ ምስጋና በምድር /2/
ለኃያሉ ጌታ ለልዑል እግዚእብሔር
አሥፈሪ ነው ያልነው ብዙ ነገር ነበር
ሁሉንም አለፍነው እግዚአብሔር ይመስገን
ሕዝቦች ደስ ይበለን ህይወታችን ድኗል
ሰይጣን ጠላታችን አፍሮ ተመልሷል
ሰማይ ዙፋንህ ነው ምድር መረገጫህ
በዚህም በዚያም ቢሆን በሁሉም አንተው ነህ
በሄድንበት ሁሉ ትከተለናለህ
ከዕንቅፋት ከድንጋይ ትሠውረናለህ
ስለመልካም ሥራህ አለብን ውለታ
ለማይነገረው የማዳን ስጦታ
ተመስገን እንበልህ ከጧት እሰከ ማታ
ሌላ ምንም የለም የምንከፍልህ ጌታ
አምላክ ሆይ ስምህን ብንጠራው ብንጠራው
አልጠገብ አለን ምንኛ ጣፋጭ ነው
አቤት ያንተ ሥራ ያንተ ልግስና
ቢነገር አያልቅም ስምህ ነው ገናና
መልስ እንድናዘጋጅ ቶሎ ሳንጠራ
ሳለ አንደበታችን ምስጋናህን ያውራ
ምስጋና በሰማይ ምስጋና በምድር
እሰከ ዘለዓለም ለስምህ እንዘምር
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.