የቅድስት ሥላሴ

Holy Trinity

ወሮታህ ብዙ ነው

Lyrics

እግዚአብሔር ሆይ ወሮታህ ብዙ ነው

ለጠራህ ሰውሁሉ ከጸጋህ ሰጠኸው

በብዙ በረከት ሕይወቱን ዳሰስከው

እግዚአብሔር አምላክ ሆይ ፍቅርህ የበዛ ነው/2/

ለድንግል ሰጠኅት ንፁሕ የሆነ ልብ

ለዳዊት አደልከው የበገናን ምሥጢር

ለያሬድ ሰጠኸው የማኅሌት ጥበብ

ታዲያ ለዚህ ሁሉ ምን ይከፈልሀል

ስጦታህን ሳስብ ውስጤ ይገረማል /2/

በኃጢአት ስንኖር አመፀኛ ሆነን

ልዩ የሆነውን ፍቅርህን አቃለን

አንተ ግን ኃጢያትን ፈጽመህ ረስተህ

የምድርን በረከት ሳትሳሳ ሰጠህ

አመፀኛውን ልብ ታስደስተዋለህ /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening