የቅድስት ሥላሴ

Holy Trinity

ሞት ነው ረሀብ

Lyrics

ሞት ነው ረሀብ ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየን/2/

ኃይሉ በእኛ ላይ አድሮ እንበረታለን

ጸጋው በእኛ ላይ አድሮ እንበረታለን

ከአንተ ርቀው ሸሽተው እየሄዱ

ጠፋባቸው የጽድቅ መንገዱ

ለሥጋዊ ጥበብ ሲፈልጉ

በመታለል ስንቶቹ አንተን አጡ

በተዋህዶ የከበርከው ጌታ

መድኃኒዓለም ሁንልን መከታ

ስንደክም ምኞት ሲፈትነን

ኃይልን ሰጥተህ በእጆችህ ደግፈን

የዓለም ሰይፍ በእኛ ላይ ተስሏል

ሥጋችንን ሊቆርጠው አድብቷል

ኃይልን ስጠን እንድናሸንፈው

ጸጋህ ለእኛ የእምነት ጋሻችን ነው

ሐዋርያት ጸጋ በዝቶላቸው

ስለፍቅር ፈሰሰ ደማቸው

ዛሬም ለእኛ ጸጋህን አብዛልን

እንዳንደክም ፈተና ሲገጥመን

ጋሻ ሆነህ እንድትመክትልን

ቸር አምላክ ሆይ ወደ አንተ እንጮኻለን

ቢገጥመንም ችግር ወይ መከራ

አትለየን ጌታ ከእኛ ጋራ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening