✦
የቅድስት ሥላሴ
•Holy Trinity
አማን በአማን
Lyrics
አማን በአማን /4/
አማኑኤል ተመስገን
ለዚህ ፍቅርህ ምን እንበል
ድብቁን ኃጢአት አንተ ብትገልጠው
ይቅር ብለኸኝ ባትሸፋፍነው
እንደ ሰው በቀል ቢኖርህ ጌታ
ለእኔ ኃጢአትስ የለውም ቦታ
በየደቂቃው ኃጢያት ስሰራ
ስሰርቅ ስበድል አንተን ሳልፈራ
አንተ ግን ፊትህ ምንም ቢቀየም
በቁጣ በትር አልገረፍከኝም
ምሕረትን ልከህ አድነኝ ዛሬ
ታክቶኛልና በኃጢያት መኖሬ
ዓለም በኃጢያት እየሳበችኝ
በጽድቅ ደስታ መኖር አቃተኝ
የኃጢያት ጉዞ ጣፋጭ ቢመስልም
ውጤቱ መሮ ፍፁም አይጥምም
እንደበደሌ ስላልከፈልከኝ
ተመስገን እንጂ ሌላ ምን አለኝ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.