የቅድስት ሥላሴ

Holy Trinity

እናመስግነው

Lyrics

እናመስግነው /2/

አምላካችን ውለታው ብዙ ነው /2/

ከኃጢአት ገደል ከሞት ቤት ለይቶ

መንግሥቱን የሰጠን ከሲዖል አውጥቶ

ዘለአለማዊ ቤት ታላቅ ሀብት ያደለን

መቼም የማይተወን ታላቅ አባት አለን

ፍጡራን ቢንቁኝ መጎስቆሌን አይተው

ወዳጆች ቢሸሹኝ ተስፋ ቢስ ነው ብለው

እውነተኛው ረዳት አምላኬ መች ተወኝ

ሁለት እጄን ይዞ ልጄ ተነስ /ሽ/ አለኝ

ሞታችንን ሙቶ ህይወትን ላደለን

ለቸሩ ክርስቶስ ምን እንከፍለዋለን

ለታላቅ ውለታው ጌታ ለዋለልን

በእልልታ እንዘምር በአንድነት ሆነን

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening