የቅድስት ሥላሴ

Holy Trinity

ከክርስቶስ ፍቅር

Lyrics

ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየን ማን ነው

መከራ ችግር ስቃይ ወይስ መራቆት ነው /2/

አንፈራም አንሰጋም አንጠራጠርም

እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ይኖራል ለዘለዓለም /2/

የሰማይ ቤታችን አማኑኤል የሰራው

ግንቡ ንጹህ ውኃ መሰረቱ ደም ነው /2/

ሳይነጋ ተራምደን እንግባ በጠዋት

በደሙ መሥርቶ ከሠራልን ቤት /2/

ከቶ የት ይገኛል እንዲህ ያለ ቤት

የውኃ ግድግዳ የደም መሰረት /2/

የውኃ ግድግዳ የደም መሰረት

ይኸው እዚህ አለ የሥላሴ ቤት /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening