የቅድስት ሥላሴ

Holy Trinity

ወደ ቤተ እግዚአብሔር

Lyrics

ወደ ቤተ እግዚአብሔር እንሒድ ሲሉኝ

እንደ ዳዊት እንደ ንጉሡ ተደሰትኩኝ /2/

መላእክት በሰማይ የሚያመሰግኑህ

አምላካችን ፈቃድህ ይሁን እንዘምርልህ/2/

ሞትን አሸንፎ ለተነሳው ጌታ

ዘምሩለት ተቀኙለት ጠዋትና ማታ /2/

በመስቀል ላይ ሆኖ ሲወጋ ጎኑን

ውኃና ደም በአንድ ላይ ሆኖ ፈሰሰልን/2/

በውኃው ተጠምቀን ደሙን ጠጥተን

መንግሥቱን እንድንወርስ ስላደረገን

ስሙ ይክበር ከፍ ከፍ ይበል የጌታችን

ስሙ ይክበር ከፍ ከፍ ይበል የአምላካችን

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening