የቅድስት ሥላሴ

Holy Trinity

በፍቅር ተስቦ

Lyrics

በፍቅር ተስቦ ወረደ ለእኛ ሲል

የፍቅሩን ፍጻሜ ገለጸው በመስቀል

ለእኛ ያላረገው ከቶ ምን አለና

አፋችን ዝም አይበል እናቅርብ ምስጋና

ደስ ይበለን ሰማያትን ቀዶ

ደስ ይበለን ታላቁ አባታችን

ደስ ይበለን የዘመናት ንጉስ ደስ ይበለን ኢየሱስ ጌታችን

ደስ ይበለን የኤፍራታው ሕፃን ደስ ይበለን በዳዊት ከተማ

ደስ ይበለን ተወልዶ ማዳኑ ደስ ይበለን ምስራች ተሰማ

እንዳንተ ያለ በኃጢአት ውስጥ ወድቀን

እንዳንተ ያለ ስንኖር ተጎሳቁለን

እንዳንተ ያለ አምላክ የእኛ ጌታ

እንዳንተ ያለ ከሞት ውስጥ አዳንከን

እንዳንተ ያለ ዝናውንም አውሩ

እንዳንተ ያለ ለአህዛብ ሁሉ

እንዳንተ ያለ እንደ እግዚአብሔር ያለ

እንዳንተ ያለ ማንም የለም በሉ

ደስ ይበለን ወረደ ወደ ምድር

ደስ ይበለን ሰላሙን ሊሰጠን

ደስ በለን ሰላም ለእናንተ ይሁን ደስ ይበለን ብሎ ሰበከልን

ደስ ይበለን በመስቀል ተሰቅለ ደስ ይበለን እኛን የተቤዠን

ደስ ይበለን ከሲዖል እስራት ደስ ይበለን በፍቅሩ የፈታን

ሃሌ ሉያ ምስጋና በሰማይ

ሃሌ ሉያ ምስጋና በምድር

ሃሌ ሉያ ሁሉን ቻይ ለሆነው

ሃሌ ሉያ ለቸሩ እግዚአብሔር

ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ለእርሱ

ሃሌ ሉያ ለነፍሳችን ጌታ

ሃሌ ሉያ ዝማሬን እናቅርብ ሃሌ ሉያ ከጧት እስከማታ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening