የቅድስት ሥላሴ

Holy Trinity

ሥላሴን አመስግኑ

Lyrics

ሥላሴን አመስግኑ /2/

የምድር ፍጥረታት ዘምሩ እልል በሉ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ

ምስጋና ይገባል ከምንም በፊት

ዓለማትን ሁሉ ለፈጠረ ጌታ

ምስጋና ይገባል ሁሌ ጠዋት ማታ

ኪሩቤል ሱራፌል የሚያመሰግኑት

መላዕክት በሰማይ የሚዘምሩለት

እኛም የአዳም ልጆች እንዘምራለን

በሰማይ በምድር እንጠራሃለን

ብራብ በሥላሴ እጠግባለሁኝ

ብጠማም በአምላኬ እረካለሁኝ

ሥላሴ አምባዬ ክብሬም ናቸውና

ሁሌም ይመሩኛል በሕይወት ጐዳና

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening