✦
የቅድስት ሥላሴ
•Holy Trinity
እግዚአብሔርን አመስግኑት
Lyrics
እግዚአብሔርን አመስግኑት ስራው ግሩም ድንቅ ነው በሉት
ሰማይን ያለምሰሶ ምድርንም ያለመሰረት ያጸናው እርሱነው
ሥራህ ግሩም ድንቅ ነው በሉት
የባሕርን ጥልቀት የመጠነ ዳርቻዋን የወሰነ
ሥራህ ግሩም ድንቅ ነው በሉት
እግዚአብሔርን አመስግኑት ማዕበል ነፋስን የሚገስፅ ፍጥረቱ ለስሙ የሚታዘዝ
ትጉህ እረኛ ድካም የሌለበት እግዚአብሔርን ስራህ ድንቅ ነው በሉት
ንጹህ ባሕርይ ነው ሁሉን የሚገዛ የነገሥታት ንጉስ አልፋና ኦሜጋ
ዘላለም እርሱ የማይለወጥ እግዚአብሔርን ስራህ ድንቅ ነው በሉት
ጥበብን የሚገልጥ ጥበበኛ ፍርድ የሚያደርግ እውነተኛ ዳኛ
እንደ እርሱ ያለ ከቶ አይገኝም እግዚአብሔር ግሩም ነው ዘላለም
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.