የቅድስት ሥላሴ

Holy Trinity

ኑ በእግዚአብሔር

Lyrics

ኑ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን /2/

ለታላቁ ክብር ለዚህ ላበቃን ከሞት ወደ ህይወት ላሸጋገረን

ኑ በእግዚአብሔር ኑ በድንግል ደስ ይበለን

የሰማዩን መንግሥት ርስቱን ለሰጠን ከጨለማ አውጥቶ ብርሃንን ላሳየን

ለዚህ ድንቅ ውለታው ምስጋና ያንሰዋል በእርሱ ደስ ይበለን ክብር ይገባዋል

ከዓለት የፈለቀ ውኃ ጠጥተናል ሰማያዊ መና አምላክ መግቦናል

ፍቅርህ የበዛ ነው ምን ልክፈልህ ጌታ ስምህን ላመስግነው ከጠዋት እስከ ማታ

በቃዴስ በረሃ ምንም በሌለበት በኤርትራ ባሕር ወጀብ በበዛበት

ለእርሱ መንገድ አለው ከቶ ምንተስኖት ልባችሁ አይፍራ በፍጹም እመኑት

በባርነት ሳለን በድቅድቅ ዓለም ብርሃንን አገኘን በድንግል ማርያም

ያጣነውን ሰላም ዛሬ አገኘን እጅግ ደስ ይበለን በእመቤታችን

የሐና የኢያቄም የእምነታቸው ፍሬ በእግዚአብሔር ፈቃድ ተወለደች ዛሬ

የኢያቄም ስእለቱ የሐና እምነት ለምኚልን ለእኛ ኪዳነ ምሕረት

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening