የቅድስት ሥላሴ

Holy Trinity

እንደ እግዚአብሔር ያለ

Lyrics

እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለምና እልል በሉ ቁሙ ለምስጋና /2/

ባሕር ተከፈተ እስኪታይ መሬቱ ፈርኦን ወደቀ አልሰራም ትምክህቱ

ደካሞቹም ጸንተው ተራመዱ ኃይልኞቹም ይኸው ተዋረዱ

የኢያሪኮ ቅጥር የማይደፈረው ይኸው ፈራረሰ የሰው እጅ ሳይነካው

ኃይለኞቹም ቢበረታቱብን እንጸናለን በእርሱ ተደግፈን

የተወረወረው የጠላታችን ጦር ሜዳ ላይ ወደቀ ጋሻ ሆኖ እግዚአብሔር

ለሥላሴ ይድረስ ምስጋናችን ተሸነፈ አዳኝ ጠላታችን

ባሕር ላይ ሲራመድ ሞገስ አለው እርሱ በግርማው ሲነሳ ጸጥ ይላል ነፋሱ

የድንግል ልጅ እኛ የምናመልከው ከሀሊ ነው የለም የሚሳነው

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening