የቅድስት ሥላሴ

Holy Trinity

ደስ ይበለን በጣም

Lyrics

ደስ ይበለን በጣም ደስ ይበለን /2/ በረከቱን ለኛ ስላደለን

በጨለማ ስንኖር በኃጢአት ተከበን የሕይወትን ብርሃን ፍቅሩን አበራልን

ወደ ምሥራቅ እንይ ፀሃይ ወዳለበት ጨለማው ልባችን ጎህ እንዲቀድበት

የፀሓይ እናቱ ማርያም እመቤቴ እለምንሻለሁ እስከ እለተ ሞቴ

የልቤ ማረፊያ የዘላለም ቤቴ አንቺ ነሽ ተስፋዬ ዕፀ መድኃኒቴ

የግሸኗ ንግስት የአምላክ እናት ሆና ተሰጥታለች ለሚመኩባት

በልቼ ጠጥቼ የምረካብሽ ጎጆ ማረፊያዬ ደስ ይበለን ደስ ይበለን

ማርያም አንቺ ነሽ ጸዓዳ እመቤቴ ሐመልማለ ሲና የሕዝቅኤል ደጃፍ የሙሴ ደመና

የተዋበች ዕንቁ የደጎች አዝመራ በማህፀንሽ ፍሬ ሕይወታችን በራ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening