የቅድስት ሥላሴ

Holy Trinity

አድርገህልኛልና

Lyrics

አድርገህልኛልና በቸርነትህ አመሰግንሃለሁ እልል እልል

ለዓለመ ዓለም አማኑኤል እገዛልሃለሁ መድኃኔአለም

ቀኑ ጨልሞብኝ ዙሪያው ገደል ሆኖ የችግሬ አረንቋ ፊቴ ተደቅኖ

ረዳት ያጣሁኝ በመሰለኝ ጊዜ ፈጽሞ አራክልኝ የልቤን ትካዜ

አምላኬ ጉልበቴ ኃይሌ መመኪያዬ ጠላት ማሳፈሪያ የእምነት ጋሻዬ

እንደማትተወኝ አሁን አውቂያለሁ ከአለኝ ነገር ይልቅ በአንተ ታምኛለሁ

ጥቂቷን አብዝተህ ለምትመግብ ጌታ የምመልስልህ ባላገኝ ስጦታ

በቀንም በሌትም ሁሌ ለሚያበራ መንክር ለባሕርይህ ዕጹብ ለአንተ ሥራ

አምላክ ሆይ ምስጋና ለአንተ ይገባሃል ለምስኪኗ ጎጆ በረከት ሰጥተሃል

ድሃ ነኝ አልልም ሀብቴ አንተ ነህና ማሰሮዬ ሞልቷል ላይጎድል እንደገና

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening