✦
የቅድስት ሥላሴ
•Holy Trinity
የሥላሴን መንበር
Lyrics
የሥላሴን መንበር ቅዱሳን ከበውት ኪሩቤል በደመና ዙፋኑን ይዘውት
ድንግል ከመሐል ሚካኤልን ከፊት አእላፍ መላእክት ሲሰግዱ በፍርሐት
እዩ ተመልከቱት የሰማዩን አባት /2/
የሥላሴን መንበር ቅዱሳን ከበውት እያሸበሸቡ የሰማይ መላእክት
ካህናተ ሰማይ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ሲሉ ይህን ታላቅ ክብር ሊያዩ የታደሉ
በፅድቅ ሥራቸው ደምቀው ይታያሉ /2/
የቅዱሳን ሕብረት የቅዱሳን ሀገር ሲያወድስ ይኖራል የሥላሴን ክብር
ጽድቅና ርኅራኄ የተሞላ ሰማይ እግዚአብሔር ያድለን በትንሣኤ እንድናይ/2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.