✦
የቅድስት ሥላሴ
•Holy Trinity
ድንቅ ነው
Lyrics
ድንቅ ነው ልዩ ነው ልዑል የእኛ ጌታ ምስጋና ይድረሰው ከጧት እስከ ማታ
የማይመረመር በሰው ልጅ ሕሊና ረቂቀ ባህርይ ገናና ነውና
ያለ የነበረ ከዘመናት በፊት ለዘለዓለም ኗሪ ፈጣሪ ዓለማት
በፍጥረታት ሁሉ የሚመሰገነው ኃያሉ ጌታችን በእውነት ግሩም ነው
በፍጹም ልዩ ነው የእርሱ ጌትነቱ አልፋና ዖሜጋ ጽኑ ነው መንግሥቱ
በመላእክት ዓለም በሰማይ ከተማ ለክብሩ ሲዘመር ማኅሌት ሲሰማ
ያለምንም እረፍት በቀንና ሌሊት ትጉኃን መላእክት የሚያመሰግኑት
አዳምን ለማዳን ፍጹም በመውደዱ የማይሞተው አምላክ ሞተ በፈቃዱ
ምስጢሩ ረቂቅ ነው ለሰዎች አዕምሮ ፍቅሩ ያስደንቃል ስናየው በአንክሮ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.