የቅድስት ሥላሴ

Holy Trinity

ማን እንደ እርሱ

Lyrics

ማን እንደ እርሱ እንደ እግዚአብሔር ቸርነቱ ብዙ በሰማይ በምድር

ሞገድና ነፋስ የሚታዘዙለት አብርሕት ቀላያት የመሰከሩለት

ኅቱም መቃብርን ሳይከፍት የተነሳ ነፍሳትን ያዳነ ከሲዖል አበሳ

ፈዋሴ ድውያን ቸርነቱ ብዙ የጸጋ ልብሳቸው ጽድቅን ለታረዙ

የተዋረዱትን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ለባልቴቷ ዳኛ ፈራጅ ለድሃ አደግ

የጠፋውን አዳም ሊፈልግ የመጣ ከባርነት ዓለም ከጽልመት ያወጣ

ብርሃን ዘበአማን ጨለማን ያራቀ ሰውን ከራሱ ጋር ሞቶ ያስታረቀ

በመከራ ሳሉ ህዝቦቹን ያሰበ ሥጋውና ደሙን ቆርሶ የመገበ

ከባቴ አበሳ ምሕረቱ የበዛ ጌታችን እርሱ ነው የሁላችን ቤዛ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening