✦
የቅድስት ሥላሴ
•Holy Trinity
ስምህ በሁሉ ተመሰገነ
Lyrics
ስምህ በሁሉ ተመሰገነ ከክብር በላይ ክብርህ ገነነ
አንተን ማወደስ ያስደስተናል ስምህን ማክበር ግብራችን ሆኗል
አምላክ ተመስገን በሰማያት ስምህ ይወደስ በፍጥረታት
ከአንደበታችን ምስጋና ይውጣ አንተን ማመስገን ይሁን የእኛ እጣ /2/
በምግብ እጦት ብንሰቃይም ማኅሌትህን አናቋርጥም
የመከራ ዶፍ ቢወርድብንም እንዘምራለን ለአምላካችን ስም/2/
ሰማዩ ዝናብ ደመና ቢያጣ ፍቅርህ በእኛ ውስጥ አላቋረጠም
ቸርነትህን እንጠብቃለን ከአንተ ደጅ አምላክ የት እንሔዳለን/2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.