የቅድስት ሥላሴ

Holy Trinity

እግዚአብሔርን ጠራሁት

Lyrics

እግዚአብሔርን ጠራሁት በሐዘኔ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት በችግሬ ጊዜ

አወጣኝ ከጭንቀት ከሓዘን ከትካዜ /2/

የልመናዬን ድምፅ እርሱ ሰምቷልና ጆሮውን ወደ እኔ አዘንብሏልና

በዘመኔ ሁሉ ስጠራው እኖራለሁ ጎስቋላ ብሆንም ምስጋና አቀርባለሁ /2/

እንደ ቃልህ መሄድ መራመድ አቅቶኝ የኃጢአቱ መንገድ ማዕበሉ ገፍቶኝ

ወደ እርሱ ስማፀን ደግሞ ስፀፀት አላሳፈረኝም መጣ በምሕረት /2/

ኖኅን እንዳዳንከው እኛንም አድነን ከቀስቱ እንድናመልጥ ምልክትን ስጠን

በትርህ ምርኩዝህ እነርሱ ያጽናኑኝ አንተ ከኔ ጋር ነህ አልፈራም ክፉውን/2/

በበዛው ምሕረቱ ያለፈውን ትቶ በፍቅሩ ጎበኘኝ አልተወኝም ከቶ

ሊቀበለኝ ወዶ ፊቱን አበራልኝ ማን ይቃወመኛል እግዚአብሔር ካለልኝ /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening