✦
የቅድስት ሥላሴ
•Holy Trinity
ዘይክል ኩሉ
Lyrics
ዘይክል ኩለ ወአልቦ ዘይስአኖ ለእግዚአብሔር
አምላከ ነዳያን ወተስፋ ቅቡፃን /ረዳኤ ምንዱባን /ናዛዜ ኅዙናን
ንሕነ ኃቤከ /2/ ተማኅፀነ
የድሆች ፈጣሪ ተስፋ ላጡ ተስፋ ሁሉንም የሚችል ደራሽ ለተከፋ
ለእኛም ድረስልን በኃጢኣት ሳንጠፋ
ከገነት ሲባረር አዳም ተሳስቶ ባለቀሰ ጊዜ ልጅነቱን አጥቶ
ትድናለህ ብለህ ያዳንከው በመስቀል የቅዱሳን አምላክ አቤቱ ቸል አትበል
ህዝበ እስራኤልን ፈርኦን ሲገዛቸው ጭንቅና መከራ እያፀናባቸው
በእነ ራሔል እንባ ሙሴን ላክላቸው እኛም ወገኖችህ ወደ አንተ እንጮሀለን
ከጭንቅ ከመከራ እንድትታደገን ጌታ አንተ ነህና ናዛዜ ኅዙናን
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.