የቅድስት ሥላሴ

Holy Trinity

ወደ ማደሪያው ገብቼ

Lyrics

ወደ ማደሪያው ገብቼ ልስገድ ለእግዚአብሔር

ምስጋናንም ላቅርብ ስለስሙ ክብር

አድርጐልኛልና አመሰግነዋለሁ

በአፀደ መቅደሱም እሰግድለታለሁ

በፊቱ ለመቆም ማልጄ እነሳለሁ /2/

በመከራዬ ቀን ሆኖኛል መከታ

ቤቱ ተገኝቼ በፍጹም ደስታ

የከንፈሬን ፍሬ ልሰዋ በእልልታ

አሥር አውታር ባለው በበገና

በመላእክቱ ፊት ለማቅረብ ምስጋና

የአፌንም ነገር ሰምተኸኛልና /2/

ለስሙ ልንበርከክ ለእርሱ እንደሚገባ

ስእለቴን ልፈጽም ላቅርብለት መባ

ወደ አደባባዩ በምስጋና ልግባ /2/

አሸበሽባለሁ ድምጼን አሰምቼ

በቤተ መቅደሱ ሌሊት ተገኝቼ

እንደካህናቱ እጆቼን ዘርግቼ /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening