የቅድስት ሥላሴ

Holy Trinity

ስለማይነገር ስጦታው

Lyrics

ስለማይነገር ስጦታው

እግዚአብሔር ይመስገን

ቸል ያላለን አምላክ ስንጓዝ

ማዕበሉን አቋርጠን

ስለማይነገር ስጦታው

እግዚአብሔር ይመስገን

የሕይወት እስትንፋስ ዘራብን

ሕያው እንድንሆን

ይህን ያደረገ አምላካችን

እግዚአብሔር ይመስገን

ስለማይነገር ስጦታው

እግዚአብሔር ይመስገን

ነፋስን ገስጾ ማዕበል

አቁሞ የሚያሻግር

የዓለም ፈተና ቢበዛ

እርሱ መጠጊያችን

ስለማይነገር ስጦታው

እግዚአብሔር ይመስገን

ዳግም እንዳንሞት በሞቱ

ሞትን የረታልን

የምንመካበት ትንሣኤ

ሰላምን ለሰጠን

ስለማይነገር ስጦታው

እግዚአብሔር ይመስገን

ከሲዖል እስራት ተፈተን

ነፃ የወጣንበት

መስቀሉን ለሰጠን ለአምላካችን

እንዘምር በእውነት

ስለማይነገር ስጦታው

እግዚአብሔር ይመስገን

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening