✦
የቅድስት ሥላሴ
•Holy Trinity
የነገሥታት ንጉሥ
Lyrics
የነገሥታት ንጉሥ ቸሩ አባት
የጌቶቹም ጌታ በሰማያት
ከቶ እንደ አንተ ማነው ሩኅሩኅ አባት /2/
ቅያሜ በአንተ ዘንድ ቸሩ አባት
ምንም ቦታ የለው በሰማያት
ፍጹም ቸርነትህ ቸሩ አባት
የአንተ ባሕርይ ነው በሰማያት
ከቶ እንደ አንተ ማነው ሩኅሩኅ አባት/2/
ምሕረትህ ለሰው ልጅ ቸሩ አባት
እጅጉን በዝታለች በሰማያት
ኃጢአት በበዛባት ቸሩ አባት
ጸጋህ ትበዛለች በሰማያት
ከቶ እንደ አንተ ማነው ሩኅሩኅ አባት /2/
የትዕግስትህ ብዛት ቸሩ አባት
እኔን ደንቆኛል በሰማያት
የኃጢአቴን ዋጋ ቸሩአባት
መቼ ከፍለኸኛል በሰማያት
ከቶ እንደ አንተ ማነው ሩኅሩኅ አባት/2/
ስንበድል ስንቀጥፍ ችሩ አባት
አንተን ተደብቀን በሰማያት
አይተህ እንዳላየህ ቸሩ አባት
በምሕረት አለፍከን በሰማያት
ከቶ እንደ አንተ ማነው ሩኅሩኅ አባት /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.