የቅድስት ሥላሴ

Holy Trinity

ዝናውን ሰምቼ

Lyrics

ዝናውን ሰምቼ ፈለኩት

በሾላ ላይ ሆኜ አየሁት

ከአንተ ጋር ነኝ አለኝ መድኃኒቴ

ዛሬ መዳን ሆነልኝ ለቤቴ

የረከሰው ቤቴን ጌታዬ ሳይንቀው

ጨለማውን ገፎ ብርሀን አለበሰው

ለገናናው ስሙ ለእርሱ ተንበርክኬ

ዛሬ ተለወጠ ጐስቋላው ታሪኬ

እንደምን ወደደኝ ምን አግኝቶ ከእኔ

ሕይወቴ ያደፈ ነው የገባው ኩነኔ

እርሱ ግን ጎበኘኝ በማዳን አዋጁ

ስሙን አተመብኝ አደረገኝ ልጁ

ካለኝ እኩሌታ ለደሃ እሰጣለሁ

የበደልኩትን ሰው በእጥፍ እክሳለሁ

የአንተ ካደረከኝ ያንተው ነኝ ብያለሁ

ንገስብኝ አምላክ እገዛልሃለሁ

የአብርሃም አምላክ የእስራኤል መና

የጠፋን ሊፈልግ ሊያድን መጥቷልና

እኔንም ጐበኘኝ በማዳኑ ጥሪ

ወሮታውን ክፈይ ነፍሴ ሆይ ዘምሪ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening