የቅድስት ሥላሴ

Holy Trinity

ወደ ቤተ እግዚአብሔር

Lyrics

ወደ ቤተ እግዚአብሔር እንሂድ

ባሉኝ ጊዜ እኔን ደስ አለኝ /2/

የኃጢአት ሽክሜ ቀለለኝ /2/

እስቲ ላነሳሳው የዳዊትን መዝሙር

አምላኬን ላመስግን በደስታ በፍቅር

በልቤ እያሰብኩኝ ለእኔ ያለውን

ፍቅር/2/

የጥፋት ማዕበል ጎጆ መከለያ

የጻድቁ የኖህ የመርከቡ አምሳያ

ቤተክርስቲያን ነች የእኛ መሸሸጊያ /2/

ወደ ቤተ እግዚአብሔር እንሂድ ሲሉኝ

መንፈስ ቅዱስ ቀርቦ ልቤን ደስ አለኝ

ጌታ ከደጃፍ ሁሉ አትለየኝ /2/

ኃጢአት እሾህ ሆኖ ቁስሉ ሲወጋጋህ

ሞት ሲያንዣብብብህ ሲጠወልግ ተስፋህ

ቤተ ክርስቲያን ሂድ መንገዷም አይጥፋህ/2/

የቅዱሳን ክብር የሚነገርባት

ድንግል ከነልጇ የምትገኝባት

ይህች ቅድስት ስፍራ ቤተክርስቲያን /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening