✦
የቅድስት ሥላሴ
•Holy Trinity
አምላክ አለ መሀላችን
Lyrics
ደስይበለን /2/
አምላክ አለ መሀላችን
ምን ይከፈል ለዚህ ሥራህ
ገናና ነው አምላክ ክብርህ
ምህረቱን አይተናልና
አድርሶናል አምላክ በጤና
ይህችን እድሜ የጨመረልን
ለንስሓ ጊዜ የሰጠን
ኃጢአትህን ይታገስሃል
በቸርነት አምላክ ያይሀል
ደስታ ነው በሰማያት
በአንድ ኃጥእ የጽድቅ ሕይወት
እልል በሉ የጎበኛችሁ
በምህረቱ አምላክ ያያችሁ
በችግር ቀን ያሰበን ሁሉ
አመስግኑ ዝምም አትበሉ
ድንግል ማርያም ታማልዳለች
ኃጥኡን ሰው ማረው እያለች
በድንግል ክብር እንኖራለን
በፅኑ ፍቅር አንድ እንዲያደርገን
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.