✦
የቅድስት ሥላሴ
•Holy Trinity
ቸሩ ሆይ
Lyrics
ቸሩ ሆይ ቸሩ ሆይ ናና
ቸሩ ሆይ አማኑኤል ናና
የእስራኤል መና ቸሩ ሆይ ና ና
ቸሩ ሆይ መድኃኔዓለም ና ና
ለዐይነ ስውር መሪ
ምርኩዝ መመኪያ ነህ
አንተን የሚመስል
ምንም ነገር የለም
ምሕረትና ፍቅርህ
ወሰን ወደር የለው
ሳንወድህ ወደኸን
ቸሩ ሆይ
ፈልገህ ጠራኸን
ሰምተህ እንዳልሰማ
አይተህ እንዳላየ
ሁሉን ታልፈዋለህ
ፍቅራዊ አባት ነህ
ኣማኑኤል ጌታ
ቸሩ ፈጣሪያችን
ውለታህ ብዙ ነው
ለእኛ የዋልክልን
በከብቶች ማደሪያ
ቸሩ ሆይ
በዚያች ትንሽ ግርግም
ተወልዶ አዳነን
ጌታ መድኃኔዓለም
እልል በሉ ሰዎች
በአንድ ላይ ዘምሩ
ስብሐት ለእግዚአብሔር
በአርያም በሉ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.