✦
የቅድስት ሥላሴ
•Holy Trinity
በበጎ ፈቃዱ
Lyrics
በበጎ ፈቃዱ ሁሉ በእርሱ ሆነ /2/
ነገር ሁሉ በእርሱ ተከናወነ /2/
ሰማይና ምድር ክብሩን ተናገሩ
ፈጥሯቸዋልና እንዲገለጥ ክብሩ
በፈጠረው ፍጥረት የሚታወቅ እርሱ
እግዚአብሔር ይመስገን ስሙን አወድሱ
አልሆነም ያለ እርሱ ፍጹም አንዳች ነገር
ብንመረምረው በሰማይ በምድር
ፈቃዱ ነውና መልካምና በጎ
ፈጥሮ አሳይቶናል ሁሉን ውብ አድርጎ
ክረምትና በጋ ሌሊትና ቀን
ሁሉን አሳይቶ ጌታ አስተማረን
ያደረገው ሁሉ እንከን የሌለው
ለዚህ ቅዱስ አምላክ ምሳሌም የለው
ያዘነውን ያውቃል ደስም ያለውን
ሁሉ በእርሱ ፈቃድ ስለሚከወን
ችግርና ደስታ ለበጎ ነውና
ይህን ያስተማረ ይድረሰው ምስጋና
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.