✦
የቅድስት ሥላሴ
•Holy Trinity
ይለመነናል
Lyrics
ይለመነናል አምላከ አብርሃም
ይታደገናል መድኃኔዓለም
ለፍጥረት ሁሉ እጁን የዘረጋ
ቸር እረኛ ነው አልፋና ኦሜጋ /2/
አብርሃም ይስሐቅን ያዕቆብን አስበህ
የማልክላቸውን ቃል ኪዳን አስታውሰህ
ደካማ ለሆንነው ሥጋ ሰልጥኖብን
አትመልስ ጌታ የምሕረት ዓይንህን
ከሰማየ ሰማይ ይድረስ ጩኸታችን
እንዘን እናልቅስ ስለበደላችን 12/
ባይመለከተን - አምላከ አብርሃም
በምሕረት ዓይኖቹ - መድኃኔዓለም
ባይዘረጉልን - አምላከ አብርሃም
የፍቅር እጆቹ - መድኃኔዓለም
ህዝበ እግዚአብሔር ሁሉ ለአምላክ ዘምሩ
አድኖናልና በሚያስደንቅ ፍቅሩ /2/
ምንም እንኳን ክህደት ቅጥፈት ቢበረታ
ስለአብርሃም ብለህ አልተውከንም ጌታ
ለቅዱሳን ያለህ ቃል ኪዳን ሲጸና
ቀስተ ደመናህን አይተነዋልና
የእስራኤል አምላክ የማታንቀላፋ
በፈቅርህ ታደገን በሞትሳንጠፋ /2/
ቃል ኪዳኑ ግሩም አምላከ አብርሃም
ምሕረቱ የበዛ - መድኃኔዓለም
ርስት ጉልታችን - አምላከ አብርሃም
የሕይወታቺን ቤዛ - መድኃኔዓለም
ሳይጠየፍ ጌታ ያደፈ ኃጢኣቴን
ከማጥ ዉስጥ አወጣኝ ታደጋት ሕይወቴን
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.