የቅድስት ሥላሴ

Holy Trinity

ንሴብሖ ለእግዚአብሔር

Lyrics

ንሴብሖ /2/ ለእግዚአብሔር

ስቡሓ ዘተሰብሓ /2/

እናመስግነው /2/ እግዚአብሔርን

ምስጉን ነው የተመሰገን /2/

ባሕሩን ተሻግረን ወንዙን ደረቁን

በጠላታችን ላይ ድሉ የኛ ሆነ

ከባርነት ቀንበር ፍጹም ነጻ ወጣን

ሕይወት የሚሆነን መና ነው ምግባችን

አስፈሪ ነው ያልነው ብዙ ነገር ነበር

ሁሉንም አለፍነው አምላካችን ይክበር

ጉልበታችን ቢዝል ፈተናው ቢበዛ

ኃይላችን ጌታ ነው የዓለሙ ቤዛ

ከዓለት ላይ ውኃ ፈልቆልን ጠጣን

ይኸን ታላቅ አምላክ ኑ እናመስግን

ሰዎች ደስ ይበለን ሕይወታችን ድኗል

ሰይጣን ጠላታችን አፍሮ ተመልሷል

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening