የቅድስት ሥላሴ

Holy Trinity

እግዚአብሔር ሆይ እርዳኝ

Lyrics

እግዚአብሔር ሆይ እርዳኝ ቸርነት አድርገህ

ዕድሜ ለንሥሐ እንደ ሕዝቅያስ ሰጥተህ

ጠማማውን ልቤን በቃልህ አቃንተህ

አላውቀውም ብሎ ሲጠየቅ ያመጸው

ዶሮ እስኪጮህ ድረስ 3 ጊዜ የካደው

የጅረት ወንዝ ነው የሰጠኸው እንባ

ጴጥሮስ ተጸጽቶ ንስሐ እንዲገባ

ጽዋው እንዳይርደሰኝ የይሁዳ ዕድል

ልጅህ ሆኖ ውሎ ኋላ መኮብለል

ጴጥሮስ ዕድለኛው አልቅሶ ተማረ

በትዕቢቱ ይሁዳ እንደወጣ ቀረ

ዘመኗን በሙሉ በዝሙት አቃጥላ

ለንስሐ ጠራት ጌታ በገሊላ

አልቅሳ ተማረች በእንባዋ ብዛት

እግሩ ሥር ተደፍታ ማርያም እንተ ዕፍረት

ዐመጸኛው ልቤ ዛሬስ መች ይተኛል

በኃጢአት በስርቆት በዝሙት ይዋኛል

ወደ ቀድሞ ግብሩ እንዳይመለስ

ፍቅርህ በእኔ ሠርፆ ኃጢአቴን ደምስስ

በደላችንን ሁሉ ሳታስብ ትተህ

በምጽአትህ ሰዓት ከጻድቃን ቆጥረህ

ነጭ ልብስ ለብሰን ሆነን ከአንተ ጋራ

በሩ ሳይዘጋ አስገባን አደራ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening