የቅድስት ሥላሴ

Holy Trinity

ሰዎች እንዘምር

Lyrics

ሰዎች እንዘምር ለአምላካችን

ከሞት ላወጣን ለአዳኛችን

እናመስግነው እንደ አቅማችን

ምሕረት ለሰጠን ለነፍሳችን

አምላክ ተአምሩን የሰራብህ

ጩኸት ድምጽህን የሰማልህ

በርጠሜዎስ ሆይ አትተወው

አዳኝ ጌታህን ተከተለው

እውርነቴን ያስቀረልኝ

ለዓይኖቼ ብርሃን የሠጠኝ

ሁሌም ከእርሱ ጋር እኖራለሁ

አዳኜን ትቼ የት እሄዳለሁ

በርጠሜዎስ ሆይ ታድለሃል

የመዳን ጸጋ ተሠጥቶሀል

እጹብ ድንቅ ነው የአምላክ ሥራ

እውር የሆነው ዓይኑ በራ

ይሄን ጌታዬን ምን ልበለው

ስለውለታው ምን ልክፈለው

ስሙን ላወድስ ላመስግነው

የአምላክ ክፍያ የበዛ ነው

አስራ ሁለት ዓመት ደም ሲፈስሽ

ሰዎች ሲንቁሽ ሲያንቋሸሸሽ

ማነው የፈወሠሽ አንቺ ሴት

ያበቃሽ ማነው ለድኅነት

እምነትሽ አድኖሻል አለኝ

ኃይል ወጣ ከእርሱ የሚያጽናናኝ

የጌታ ልብሱን ብዳብሰው

ደሜ ቀጥ አለ ላወድሰው

በቤተ ሳይዳ በአልጋ ስትኖር

በመጠመቂያው በወንዙ ዳር

ድውይ ስትሆን በሽተኛ

እንዴት ተፈወስክ አውጋን ለእኛ

አልጋ ታቅፌ ስንገላታ

መዳን ትሻለህ አለኝ ጌታ

አምላኬ እርሱ ፈወሰኝ

አልጋህን ይዘህ ሂድ አለኝ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening