የቅድስት ሥላሴ

Holy Trinity

ሰዎች ደስ ይበለን

Lyrics

ሰዎች ደስ ይበለን በአምላካችን

ከኃጢአት ባርነት ነፃ ላወጣን

ተነሱ እናመስግን ውለታው ብዙ ነው

ምን ይከፈለዋል ተመስገን ብቻ ነው

በኃጢአት በሽታ ወድቄ ሳለሁኝ

መድሃኒት ክርስቶስ ከውድቀቴ አነሳኝ

ስጦታው ብዙ ነው ለኔ የሰጠኝ

ተመስገን ብቻ ነው አምላክ ላንተ ያለኝ

እንደ በርጤምዮስ እውር የነበርኩኝ

ዛሬ ግን በአምላኬ ድህነት አገኘሁኝ

ህጉም ለመንገዴ ብርሐን ሆኖኛል

የእርሱ ስለሆንኩኝ ሠላምን ሰጥቶኛል

በድንቅ አጠራርህ በፍቅር የጠራኸኝ

ከአጋንንት እሥራት ነፃ ያወጣኽኝ

አልፋና ኦሜጋ ዘላለም የምትኖር

ኤልሻዳይ የሆንከው አማኑኤል ተመስገን

የዕዳ ደብዳቤዬን ጌታዬ ቀደደው

የማዳኑን ሥራ በአይኔ አይቻለው

ቸርነቱ አያልቅም ድንቅ የሆነ ጌታ

ስሙን እናመስግን እንዘምር በእልልታ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening