✦
የቅድስት ሥላሴ
•Holy Trinity
ዝናው በዓለም
Lyrics
ዝናው በዓለም የተወራ
ክብሩ በምድር የተፈራ
ምን ይሳነዋል ከቶ ለሱ /2/
እልል በሉለት በቤተ መቅደሱ
ካህናቶቹ ጽድቅ የለበሱ
በደብረ ጽዮን በራ መቅደሱ
ወደ እርሱ መጥቶ ሁሉ ተፈወሰ
ስሙን የያዘ ቀንቶት ተመለሰ /2/
መንጦላዕቱን በእሳት የሰራ
የአርያም ፀሐይ ለዓለም አበራ
ቸር አምላካችን ስንለው ሰምቶ
ይታደገናል እጁን ዘርግቶ /2/
ለሚቃወሙት ክንዱን ገለጠ
እኛን ለማዳን ሞትን መረጠ
ከደሃ ሰው ጋር ትሁት ይሆናል
ኃይለኞቹንም ያንበረክካል /2/
እግዚአብሔር ማነው ብለው ቢያሙት
እነ ፈርኦን ቢያቃልሉት
እረኛው ሙሴን ከኮሬብ ጠርቶ
አደቀቃቸው ክንዱን አንስቶ /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.