የቅድስት ሥላሴ

Holy Trinity

ገና እንዘምራለን

Lyrics

ገና እንዘምራለን ገና እንዘምራለን /2/

እንደ መላእክቱ ብርሃንን ለብሰን ገና እንዘምራለን

ወላዲተ አምላክን ከፊት አስቀድመን

በዳዊት በገና መሰንቆ ታጅበን

ለሥላሴ ክብር ገና እንዘምራለን

ገና እንዘምራለን

በምስጋና ሥራ ከሰለጠኑት ጋር

ልብን የሚያስደስት መዝሙር እየዘመርን

ያልተሰማ ዜማ ያልታየ ምስጋና

ይፈልቃል አይቀርም ከእኛ ልቡና

ገና እንዘምራለን

በትዕቢት ሳይሆን በታላቅ ተህትና

በልዩ ተመስጦ በፍቅር ልቡና

ስራችን ይሆናል ለአምላክ ምስጋና

ገና እንዘምራለን

ዳዊት በተመስጦ እርቃኑን ቢሆንም

ሜልኮን በዝማሬው ብትስቅበትም

አምላክን ወደደ እንዲያመሰግነው

በደስታ እዳይዘምር ከልካዩ ሰው ማነው

ገና እንዘምራለን

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening