የቅድስት ሥላሴ

Holy Trinity

እልል በሉ

Lyrics

እልል በሉ በአንድነት ዘምሩ

አመስግኑ ለክብሩም ዘምሩለት

እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም በሉ

በኃጢያት ባርነት ስንኖር ተገዝተን

ከቤቱ ስንርቅ ትእዛዙን አፍርሰን

አይቶ ዝም ላለን ጠላቶቹ ሳለን

ውለታው ግሩም ነው ክብር ለእርሱ ይሁን/2/

ራሱን አዋርዶ እኛን አከበረን

ሥጋውና ደሙን ብሉ ጠጡ አለን

መልካም እረኛ ነው የሚያሳጣን የለም

ምስጋና ይድረሰው ለመድኃኔዓለም /2/

ሕይወቱን የሠዋ እንደ አምላክ ማን አለ

ለሰው ልጆች ብሎ በመስቀል የዋለ

ፍቅሩም አይለካ አያልቅም ቢወራ

ከሰማያት ወርዶ ሆነከ እኛ ጋራ 12/

ሥራውን እናድንቅ እንዲህ ለወደደን

ከማያልቀው ፍቅሩ በረከት ላደለን

ለማይነገረው ለአማላክ ስጦታ

ውዳሴን እናቅርብ እንዘምር በእልልታ /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening