የቅድስት ሥላሴ

Holy Trinity

እውነተኛው ሰላም

Lyrics

እውነተኛው ሰላም ያለው ከቤትህ ነው /2/

እርደኝ አልናወጽ እለምንሃለሁ /2/

ኃጢአቴን ሳስበው ልቤ ይጨነቃል

ከአንተ መለየቴ ነፍሴን አድክሟታል

ወደ አንተ መልሰኝ እኔ እመለሳለሁ

እውነተኛው ሰላም ያለው ከቤትህ ነው

ለቅዳሴው ጸሎት ዘወትር እንዳልተጋሁ

በአደባባይ ቆሜ ስምህን እንዳልጠራሁ

ተሰነካክዬ ወድቄአለሁና

እርዳኝ አማኑኤል በሃይማኖት ልጽና

ዓይኔ እንባ ያመንጭ ላልቅስ ስለ ኃጢአቴ

የንስሓ ትሁን ቀሪዋ ሕይወቴ

በመዳኔ ሰዓት በዛሬዋ እለት

ፍቅርህን አስቤ መጣሁ ከአንተ ፊት

ጌታ ሆይ ጸጸቴን እንባዬን ተቀበል

አባትህ ነኝ በለኝ እኔም ልጅ ነኝ ልበል

ዘይት ሳላዘጋጅ ድንገት መጥተህብኝ

በርህን በመዝጋት ከደጅህ አታስቀረኝ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening