የቅድስት ሥላሴ

Holy Trinity

ንሴብሖ ለሥላሴ

Lyrics

ንሴብሖ ለሥላሴ /2/

ክበር ተመስገን አምላከ ሙሴ /2/

የእኛ አማላጅ እናታችን /2/

ነይ ነይ ወደኛ እመቤታችን

ፈጥነሽ ተገኚ በመሃላችን

ና ወደኛ ሚካኤል /2/

መልአከ ምክሩ ለልዑል

ከእግራችን ይውደቅ ሳጥናኤል

ና ወደኛ ገብርኤል /2/

ከእሳቱ አውጣን ከነበልባል

በክንፍህ ጥላ እንከለል

ና ወደኛ ዑራኤል /2/

እንደ ቅዱስ እዝራ ሱቱኤል

ጥበብን ስጠን ማስተዋል

ና ወደኛ በፈረስ /2/

የልዳው ፀሐይ ጊዮርጊስ

ገድልህን ሰምተን እንፈወስ /2/

ና ወደኛ ተክለሃይማኖት /2/

ይጠበቀን ያንተ ጸሎት ጸንተን እንድንቆም በሃይማኖት/2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening