የቅድስት ሥላሴ

Holy Trinity

እንዳንተ ማንም የለም

Lyrics

እንዳንተ ማንም የለም ከቶ የሚመስልህ

አምላክ ሆይ ድንቅ ሥራህ

አዳምን ከነልጆቹ ልታድን በገባኸው ቃል

አዳንከው እንደ ቃልህ ተወልደህ ከድንግል

ቅድመ ዓለም የነበርክ ያለህና የምትኖር

ልዑለ ባሕርይ ሕያው እግዚአብሔር

ብሥራታዊ መልአክ ቅዱስ ገብርኤልን

ላከው የመምጣህን ዜና እንዲሰብክልን

ሙሴን የተናገርኸው በእሳቱ ነበልባል

የመላእክትን ክብር የሰማዕታት አክሊል

ከሰማያት ወረድክ እንደ መንኮራኩር

ዓለምን ለማዳን ከድንግል ተወልደህ በረቀቀው ምሥጢር

በፍጡራን ሕሊና የማትመረመር

ድንቅ ነው በእውነት የሕድረትህ ነገር

የአዳም ተስፋ ነህ የሕይወት መገኛ

ክርስቶስ ሥጋችንን ለብሰህ ተወለድክልን ለኛ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening