የቅድስት ሥላሴ

Holy Trinity

ሰብሕዎ ለአምላክነ

Lyrics

ሰብሕዎ ለአምላክነ ሀሌሉያ ለእግዚአብሔር/2/

በሰማይ በምድር /6/

ሰማዩን ያለምሰሶ አጽንቷል በቃሉ

መሬትን በውኆች መሐል መሥርቷል ጥበቡ

ይታያል ያበራል ጌታ ዛሬም በሥራው

ምስጉን ነው ሠራዊት ሁሉ ያመሰገነው

ምሕረቱ ይቅርታው ብዙ ከወሰን የሰፋ

አባት ነው ብርቱ መጠጊያ የሰው ልጆች ተስፋ

መጋቢ ለፍጥረት ዓለም ታላቅ ባለጸጋ

ያብባል ይለመልማል እርሱን የተጠጋ

ተመስገን /2/ ይላል የተገጎበኘ ሰው

ከጥፋት ከጉስቁልና ከሞት የመለሰው

ይቀባል ከታች አንስቶ ከእረኝነት ቦታ

ይቅርታው ጸጋው ብዙ ነው ምሕረቱ የጌታ

መላእክት በላይ በሰማይ ይዘምሩለታል

ዳዊትም ከበገናው ጋር ለቅኔ ተነስቷል

በምድርም እኛ ልጆቹ እንበል ንሴብሖ

ይገባል ለአምላከ እስራኤል ውዳሴ አምኆ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening