የቅድስት ሥላሴ

Holy Trinity

የሕይወቴ መታመኛ

Lyrics

የሕይወቴ መታመኛ የነፍሴ ተስፋ ቤዛዬ አምላኬ ጌታዬ

መድኃኔዓለም ላመስግንህ እጠግባለው በውዳሴህ

መላዕክቱ በሰማያት ቅዱስ /3/ አንተ ነህ እያሉ

በክንፋቸው አሸብሽበው ይጠሩሀል በዝማሬያቸው /2/

ቅዱስ ዳዊት በበገና በእስራኤል ሀገር /2/

በተመስጦ ወደ አርያም ዘልቆ ዘመረልህ አንተነትህን አውቆ /2/

ሕጻንትም አንተን አምነው በአህያ ተቀምጠህ ስትመጣ/2/

አፍ አውጥተው አመሰገኑህ ሆሳዕና በአርያም አ/2/

ሀሌ አለ ቅዱስ ያሬድ ጸናጽል መቋሚያ አንስቶ/2/

ምስጋናህን ከልቡ ሽቶ በመንፈስህ በአንተ ተመርቶ/2/

ፈለጉንም ተከትለው ካህናት በሙሉ

ይቀኛሉ ለቅዱስ ስምህ በማኅሌት በመመስገኛህ /2/

እስትንፋስም ያለው ሁሉ ያመስግንህ አንተን በእውነት /2/

ከልብ ሆኖ በንጹሕ እምነት እንደ ዕዝራ እንደ ዳዊት

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening