✦
የቅድስት ሥላሴ
•Holy Trinity
ከወገኔ ጋራ
Lyrics
ከወገኔ ጋራ እዘምራለሁኝ
በደስታ በሐሴት ስሙን እጠራለሁኝ
ምግብና መጠጤ አምላኬ ነውና
ዘወትር አቀርባለሁ ለጌታ ምስጋና /2/
ሕዝቡ ተስብስቦ በቤተክርስቲያን
ሲዘምር ደስ ይላል በአንድነት ሆነን
በረከት የሞላው ዝማሬ ይገርማል
ከእጣኑ ጋር ወደ ላይ ይወጣል /2/
ቀሳውስቱ ሌሊት ማኅሌት ሲያቀርቡ
ከመላእክት ጋራ ወረብ ሲወርቡ
ብርሃን ለብሰን በድሰታ ስንዘምር
ትዝታው ልዩነው ህሊና ሲሰውር
ራእይ ነውና ኑና ተመልከቱ
ሰዎች ሲዘምሩ እንደ መላእክቱ
የፅጌው ዝማሬ የትንሣኤው ደስታ
ልዩ ዝማሬነው እንዳይመስለን ተርታ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.