የቅድስት ሥላሴ

Holy Trinity

አቤቱ ፈጣሪያችን

Lyrics

አቤቱ ፈጣሪያችን መድኃኒታችን አምላካችን አባታችን

በአንተ ላይ ነው ዘለዓለም ተስፋችን

ቀንና ሌሊቱን የምታፈራርቅ

አምላክ አንተ ብቻ ሥራህ የሚያስደንቅ

መዓትህ የራቀ ምሕረትህ የበዛ

በረቂቅ ሥልጣንህ ሁሉን የምትገዛ

በበደልነው በደል በሠራነው ሥራ

በትሕትና ፈጸምክ ያን ሁሉ መከራ

ጠላት በተንኮሉ እንዳያጠምደን

በሕይወት ጎዳና ወደአንተ ምራን

የዘለዓለም አባት የፍቅር የሰላም

አቤቱ ተመስገን እስከ ዘለዓለም

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening