የቅድስት ሥላሴ

Holy Trinity

በማስተዋል እንዘምር

Lyrics

እግዚአብሔር በምድር ሁሉ ንጉሥ ነውና

በማስተዋል እንዘምር እናቅርብለት ምስጋና/2/

ቅዱስ ዳዊት በተመስጦ ሲዘምር

በሳኦል ላይ ዘወትር የሚያድር

ርኩስ መንፈስ ይለቀው ነበር

ቅዱስ ጳውሎስ በአደባባይ መሠከረ

በእስር ቤትም ሆኖ በማስተዋል ዘመረ

ከልብ በማመስገኑም የወኅኒው በር ተሰበረ

አስተውሎ የሚዘምር ቅዱስ ያሬድን አንዘንጋ

አልታወቀውም ደሙ ሲፈስ በጦር እግሩ ሲወጋ

በተመስጦ ደርሷልና ከአልፋና ዖሜጋ

ከፈጣሪ ዘንድ እንዲደርስ ጸሎታችን

በማስተወል እናመስግን የእውነት ይሁን ዝማሬአችን

በማስተዋል እንዘምር ከልብ ይሁን ምስጋናችን

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening