የቅድስት ሥላሴ

Holy Trinity

ስብሐት ለአብ

Lyrics

ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ

ለአብና ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስም

ምስጋና ከማቅረብ ከማቶ አንወሰንም /2/

ዛሬም ወደ ፊትም ደግሞም ለዘለዓለም

ከዚህ ከማራኪው ከአስጨናቂው ዓለም

የጠራ ይድናል የፈጣሪውን ስም /2/

በእውነት ያለ ሀሰት ያለ ጥርጥር

ከቶ መድኃኒቱን የሚጠላ የለም

ኑሮአችን እንዲያምር አንድነታችንም/2/

ሊኖረን ይገባል ፍቅርና ሰላም

ያልከውን አስበህ እናንተ ሁላችሁ

ሁለት ሦስት ሆናችሁ በስሜ ካላችሁ /2/

እኔም እገኛለሁ በመካከላችሁ

አቤቱ አምላክ ሆይ እንለምንሃለን

እንድትገኝልን በመካከላችን /2/

ይኸው ተገኝተናል ሁለት ሦስት ሆነን

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening