የቅድስት ሥላሴ

Holy Trinity

እምነት ተስፋ ፍቅር

Lyrics

እምነት ተስፋ ፍቅር ከሌለኝ ለእኔ በምድር

መሥራት ከንቱ ነው ምግባር ትንቢት መናገር ምሥጢር/2/

እምነት ከሥራ ቢኖረኝ ፍቅር ከሌለኝ ከንቱ

እንደ ሚጮህ ነሀስ ሆኛለሁ ባዶ ዕቃ ሆኜ እቀራለሁ/2/

ያስታግሳል ፍቅር ያስተዛዝናል ፍቅር

አያቀናናም ፍቅር አያስመካም ፍቅር

አያስታብይም ፍቅር ክፉ አያሠራም ፍቅር

እውነት ይወዳል ፍቅር ዐመፅ ይጠላል ፍቅር/2/

ያለኝን ሁሉ ባካፍል ሥጋዬን ከእሳት ብጥል

ፍቅር ከሌለኝ አይጠቅምም ከዳግም ጥፋት አልድንም/2/

ትንቢትም ቢሆን ይቀራል

ልሳንም ቢሆን ይሻራል

ዕውቀትም ቢሆን ይጠፋል

ጉልበትም ቢሆን ይደክማል /2/

እምነት ተስፋ ፍቅር የእነዚህ ሦስቱ ነገር

ፀንተው ይኖራሉ በምድር ከሁሉ በላይ ፍቅር/3/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening