✦
የቅድስት ሥላሴ
•Holy Trinity
እግዚአብሔር ሆይ እወድሀለሁ
Lyrics
እግዚአብሔር ሆይ እወድሀለሁ ስለስምህ እቃጠላለሁ
ፍቅርህ እኔን ይመስጠኛል እንደ እግዚአብሔር ከየት ይገኛል
ዓለም ሁሉ በጠላኝ ጊዜ ስንገላታ ይዞኝ ትካዜ
አንተ ከኔ አልተለየህም እግዚአብሔር ሆይ ወደር የለህም /2/
ሳኦል እኔን ሲያሳድደኝ ጎልያድም ሲዝትብኝ
ግርማ ሆነህ ከፊቴ የቆምክ እግዚአብሔር ሆይ ስምህ ይባረክ /2/
ሞቷል ብለው ቀብረውኝ ሰዎች ምስኪን ሆኜ ሳይኖረኝ አንዳች
ከመቃብር ለይቶ አወጣኝ አይዞህ ብሎ አምላክ አፅናናኝ /2/
ሀሳብህን በእግዚአብሔር ላይ ጣል ለዘለዓለም ያበራልሀል
ታማኝ ወዳጅ እርሱ ነውና ሰላም ይሙላህ ለእርሱ ተውና /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.