✦
የቅድስት ሥላሴ
•Holy Trinity
በከሀሊነቱ
Lyrics
በከሀሊነቱ በአምላክነቱ /2/
ይቅር ይለናል ይታደገናል /2/ በቸርነቱ
ምን ይከፈለዋል ምን ይሆን ዋጋው
ለፈጠረን ጌታ ለይቅር ባይው
ለድኅነት መንገድ ንሰሐን የሠራ
እንዳንጠፋበት ነው ዳግም በመከራ
ይቅር ይለናል ይታደገናል /2/ በቸርነቱ
የሰው ልጅ ከኃጢያት እስኪመለስ ድረስ
አይቸኩልም እርሱ መዓትን ለማድረስ
ትዕግስቱ ሰፊ ነው ሥራው ረቂቅ
ቸርነት ገንዘቡ ቢሰጠው አያልቅ
ይቅር ይለናል ይታደገናል /2/ በቸርነቱ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.