የቅድስት ሥላሴ

Holy Trinity

አኮቴት ለአንተ ይገባል

Lyrics

አኮቴት ለአንተ ይገባል

ስብሐት ለአንተ ይገባል

አምልኮ ለአንተ ይገባል

ስግደትም ለአንተ ይገባል

ቅድመ ዓለም የነበር በታላቅ ሥልጣኑ

ለኩነተ ሥጋ የመጣው በፍቅሩ

ደግሞም ይህን ዓለም የሚያሳልፍ ጌታ

ኢየሱስ ክርስቶስ ኃያል የኛ አለኝታ

በሥጋው ሲታመም ሊሞት በመስቀል

በአብ ቀኝ የነበረ በሰማይ ሳይጎድል

የአዳምን ባሕርይ ተዋሕዶ ሲያከብር

በዚህ ይገለጣል የጌታችን ፍቅር

ከቅድስት ሥላሴ የማይለይ ምክሩ

ጉድለት የለበትም ትክክል ነው ክብሩ

የአብ ቃል ጥበቡ ክንዱ ስለሆነ

ዓለምን ፈጠረ አዳምን አዳነ

ሊቃነ መላእክት ኃይላቸው ነውና

ያመሰግኑታል በታላቅ ትህትና

ዘውዳቸው ክብራቸው ስለሆነ እርሱ

ይኖራሉ ወልድን ስሙን ሲያወድሱ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening